የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ ህጋዊ አሰራርን የተከተለ እና ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት ያማከለ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ስራ ማከናወን፤ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት የተቀናጀ የመሬት መረጃ አያያዝ እና የመሬት ባንክ ስርዓት በመዘርጋት፣ የመብት ፈጠራ ስራን በማከናወን ፍትኃዊ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፡

ዕይ

2025 ዓም ዘመናዊ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ስርዓት የተዘረጋበትና የላቀ አገልግሎት የሚሰጥበት እና የተገልጋይ እርካታ የተረጋገጠበት ተቋም ሆኖ ማየት።

እሴቶች

አሳታፊነት፣

ግልፅነት

ፍትሀዊነት

የላቀ አገልግሎት መስጠት

በኃላፊነት ስሜት መስራት

- ተጠያቂነት

የተቋሙ የትኩረት መስኮች  

የመልሶ ማልማት እና ወሰን ማስከበር ሥራዎችን ውጤታማነት ማረጋገጥ

የመሬት ዝግጅት፣ ባንክ እና ማስተላለፍ ስርዓት ውጤታማነትን ማረጋገጥ

የመብት ፈጠራ ስርዓትን ማሻሻል

የአገልግሎት አሰጣጡንና የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱን ማዘመን